የመጋቢው መልእክትውድ የድህረ ገጻችን አንግዶች፦ የተወደደውን ጊዜአችሁን ሰውታችሁ በአስተውሎት እየተመለከታችሁን ሰለሆነ በተወደዱ የቤተ ክርስቲያናችን አባላት ስም ከልብ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ቤተ ክርስቲያናችን ከዋናው የሴንት ፖል (Saint Paul) አጥቢያችን በእናት እና ልጅ የቤተ ክርስቲያን ተከላ መርሃ ግብር በፍቅር በ 2021 የተተከለች ስትሆን በአሁኑ ሰዓት ከልጅነት አድጋ ከዋናዋ አጥቢያ ጋር በታናሽ እህትነት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በመሆን በክርስቲያን ሚሽነሪ አላያንስ (Christian Missionary Alliance) ጥላ ስር በቅርብ አጋርነት የወንጌልን ስራ የምትሰራ ልዪ ልዪ ፈተናዎች አልፋ፦ አንደ ኮቨድ 19፣ መንፈሳዊ ውጊያዎችን፣ የወሬ ማእበልን፣ አንዲሁም የገሃነምን ደጆች ተቋቁማ በጌታ ላይ ተደግፋ የመንግስቱን ስራ የምትስራ የክርስቶስ ሙሽራ ነች። ጽናት መታወቂያቸው የሆኑ አባሎቻችን ዘወትር የእግዚአብሔርን መገኘት ከመናፈቅ ዉጭ ሌላ ጥማት የሌላቸው ሲሆን መጥተው ለሚጎበኙን ሁሉ በራችን የተከፈተ ነው። የቤተ ክርስቲያናችንን ሙሉ ዓላማ እና አጀማመር በዚሁ ድህረ ገጽ ላይ አንዲቃኙ አደራ አላለሁ።ዘወትር አሁድ ከ 10፡30 ኤም - 12፡30 ፒም ጎራ ቢሉ የማይጠገብ አምልኮ ከአምልኮ ቡድናችን አንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል ከመጋቢው እና ከሌሎች ወንድሞች አና አልፎ አልፎ ከታጋባዥ አንግዶች ይካፈላሉ። ጸሎት አና ህብረት የቤተ ክርስቲያናችን አካል ናቸው። ዘወትር ረቡእ ከ 6፡00 ፒም - 8፡00 ፒም ልዪ የሆነ ሁሉን የሚያሳትፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በወጣቶች ይቀርባል። በቤተ ክርስቲያናችን ሲገኙ አባል አንዲሆኑ ምንም አይነት ግብዣ አይደረግሎትም። በጌታ አዲስ ካልሆኑ በስተቀር ደጋግመው በመካፈል አባል የሆኑበት ቤተ ክርስቲያን ከሌለ እና በዝውውር ወይም በሌላ ምክንያት ከአኛ ጋር አብረው ለመሆን ከፈለጉ በደንብ ከተረጋጉ በኋላ መጋቢውን ወይም ሽማግሌዎችን ማናገር ይችላሉ። በ 2024 ደቀ መዝሙር በመሆን ሌሎችን ደቀ መዝሙር የማድረግ ዓላማ ይዘን ለመስራት ከጌታ ጋር አቅደናል። |
The pastor's messageDear guests of our website: On behalf of our beloved members of our church, I sincerely thank you for watching and following us attentively. Our church was planted with love in 2021 from our main parish of Saint Paul (Saint Paul) through the mother and child church planting program. Currently, it has grown from a child and has become a small sister local church with the main parish under the umbrella of Christian Mission Alliance. Our Church is a bride of Christ which has overcome many challenges: covid 19, spiritual battles, storms of rumors, and even the gates of hell, by leaning on the Lord and doing the work of the kingdom. Our steadfast members have no other thirst than longing for God's presence, and our door is open to all who come and visit us. I encourage you to explore the full purpose and beginnings of our church on this website.Every Sunday from 10:30 am to 12:30 pm, we have insatiable worship from our worship team, as well as the word of God from the pastor and other brothers and occasional guests. Prayer and fellowship are part of our church. Every Wednesday from 6:00 p.m. - 8:00 p.m., an inclusive Bible study is offered by the youth. When you attend our church, you are not obliged to become a member. Unless you are new to the Lord, if there is no church you have been a part of and you want to be with us through transfer or other reasons, you can talk to the pastor or the elders after you have settled down. We plan to work with the Lord with the goal of making disciples by 2024. |
|
|
ፓስተር አለሁበል ከበደ ማሞ
| ||