About Us


Our Values (አሴቶቻችን)

Our values are abundance, renewal, giving, presence, prayer, faithfulness, generosity, worship, service, and love.

አሴቶቻችን መብዛት፣ መታደስ፣ መስጠት፣ መገኘት፣ ጸሎት፣ ታማኝነት፣ ሰጪነት፣ አምልኮ፣ አገልጋይነት እና ፍቅር ናቸው።

Our Vision (ራእያችን)

To see ministers living and growing in the Minneapolis area making disciples, proclaiming Christ, using various ministries and graces, influencing others in serving. And to see believers who have grown in all things.

በሚኒያፖሊስ አካባቢ ደቀመዛሙርት በማፍራት፣ ክርስቶስን በማወጅ፣ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች አና ጸጋወች በመጠቀም የሚደኑ እና አድገው በሌሎች ላይ ተጽእኖ የሚያመጡ እና የሚተርፉ አገልጋዮች ማየት። እንዲሁም በነገር ሁሉ ያደጉ ምእመናንን ማየት።

Our Mission (ተልእኮአችን)

Reaching people with the power of the gospel by spreading God's kingdom and producing disciples who produce disciples. In other words, it is saving people, raising them and empowering them for service.
Matthew 22:37-38 Matthew 28:29

የእግዚአብሔርን መንግስት በማስፋፋት ደቀመዛሙርት የሚያፈሩ ደቀመዛሙርት በማፍራት በወንጌል ኃይል ሰዎችን መድረስ። በሌላ አነጋገር ሰዎችን ማዳን፣ ማሳደግ እና ለአገልግሎት ማብቃት ነው።
ማቴዎስ 22፡37-38 ማቴዎስ 28፡29


ዕብ 13:8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬም ለዘላለምም ያው ነው።
Heb 13፥8 Jesus Christ is the same yesterday, today, and forever. (NKJV)


ዓላማዎቻችን

የሚኒያፖሊስ ጽዮን ኢትዮጵያዊያን ወንጌላዊት ሕብረት ቤተክርስቲያን በሚኒያፖሊስ ዓላማዎች


❖ ቤተክርስቲያን ተከላ ሲሆን ይህም ለወንጌል ስርጭት ዋነኛ መንገድ እና ውጤታማ ነው።
❖ ብዙ አገልጋዬች በአጥቢያ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ስላሉ በተሰጣቸው ጸጋ ማገልገል እንዲችሉ በር ለመክፈት።
❖ ምእመናን ተልእኮ ተኮር አንዲሆኑ እና በአንድ ቦታ ከመቀመጥ እና ከመሟሟቅ ይልቅ መውጣት እና መንቀሳቀስ እንዲማሩ።
❖ ተልእኮአችን ሊፈጸም ወደ ሚችልበት፣ ሰዎች ወዳሉበት ቦታ ቤተክርስቲያን መሄድ ስለሚገባት።
❖ ለቤተክርስቲያን ተከላ አመቺ በሆነ ስፍራ እግዚአብሔር ሕንጻ ስለሰጠን። ለሴንትፖል ሚድዌይ መሀል እንደሆነ ለሚኒያፖሊስ ፍራንክሊን ዋና ቦታ ነው። በአገልግሎት ዘመናችን ያየነውና የሚሆን ጉዳይ ስለሆነ።

Our Goals

Minneapolis Zion Ethiopian Evangelical Union Church in Minneapolis Goals


❖ The church is a planting, which is the main and effective way to spread the gospel.
❖ There are many ministers in our local church to open doors so that they can serve with the grace they have been given.
❖ For the faithful to become mission-oriented and learn to get out and move instead of sitting in one place and getting absorbed.
❖ Because the Church needs to go where people are, where our mission can be fulfilled.
❖ Because God gave us a building in a suitable place for church planting. Franklin is a prime location for Minneapolis as Midway is for Saint Paul. Because it is an item that we have seen in our ministry.

ልቀት

የዚህችን ዓለም ልጆች የሚበልጥ ትጋት በማሳየት በነገር ሁሉ እድገት በማሳየት አንደ ጨው እና ብርሃን መታየት። ተማሪው በትምህርቱ፣ ነጋዴው በንግዱ፣ ሰራተኛው በስራው፣ እና አገልጋይ በአገልግሎቱ።

Excellence

To live as salt and light, showing greater diligence to the children of this world, and progressing in all things. The student by his education, the merchant by his business, the laborer by his work, and the servant by his service.

 


መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቱ እና አመለካከት



      ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ሕንጻ እና ቤተመቅደስ ናት     ማቴዎስ 16፡16-18     1ኛ ቆሮንቶስ 3፡9-17 እና 6፡1     እንዲሁም 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡6     ኤፌሶን 2፡19-22

      ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽሪት ናት     2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2     ኤፌሶን 5፡25-32     ዮሐንስ 14፡ 1-3     ማቴዎስ 25፡1     የዮሐንስ ራእይ 19፡7

      ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ዓለማ ያለባት እና የሚሰራባት ናት     ኤፌሶን 4፡11-14     የሐዋርያት ሥራ 6፡1-7



Biblical basis and perspective



      The church is God's building and temple     Matthew 16፡16-18     1st Corinthians 3፡9-17 and 6፡17     Also 2nd Corinthians 6፡6     Ehpesians 2፡19-22

      The Church is the bride of Christ     2nd Corinthians 11፡2     Ehpesians 5፡25-32     John 14፡ 1-3     Matthew 25፡1     Revelation of John 19፡7

      The church is where the spiritual world exists and works     Ephesians 4፡11-14     Acts 6፡1-7

 


ወደ ጎላችን የሚያደርሱን እቅዶች

✓ የእሁድ እና የሳምንቱ አጋማሽ አገልግሎቶች።
✓ ደቀመዝሙር የማድረግ ትምህርቶች።
✓ ልዩ ልዩ የመሰረታዊ ክርስትና ትምህርቶች።
✓ ወንጌል ስርጭት፣ ምስክርነትና እንዲሁም ጸሎት።
✓ የመነቃቂያ ኮንፍራንሶች።
✓ ወደ ሕብረተሰቡ የሚያስገቡ የኮሚኒቲ ስራዎችን መስራት፣ አንደተለመደው ኮሚኒቲውን መመገብ፣ ቀላል የእንግሊዝኛ ትምህርቶች፣ መሰረታዊ የኮምፒዩተር እና የመሳሰሉትን ማቅረብ።

Plans that will lead us to our goal

✓ Sunday and Midweek services.
✓ Discipleship Lessons.
✓ Miscellaneous Basic Christian Teachings.
✓ Evangelism, testimony and prayer.
✓ Motivational conferences.
✓ Doing community work that brings us into the community, feeding the community as usual, providing simple English lessons, basic computer skills and so on.

Our 2024 Goals (የ 2024 ግቦቻችን)

✓ 6000 Tracts (ትራክቶች)
✓ 40 Disciples Trained (ደቀ መዛሙርትን ማሰልጠን)
✓ 10 New People (አዲስ ነፍሳት)
✓ 5 Orphans (ወላጅ አልባ ልጆች)
✓ 2 House Churches (የቤት ቤተ ክርስቲያኖች)
✓ 1 New Ethiopian Church (አዲስ የኢትዮጲያ ቤተ ክርስቲያን)